By ለገሰ ዋንሳሞ ዋቃዮ, Hawassa, Sidama
ግንቦት 16 ቀን 1994 ዓ/ም የሲዳማ ህዝብ ህገ መንግስታዊ መብቱን ለማስከበር ህግንና ደንብን ጠብቆ በተወካዮቹ አማካይነት በቀን 12/09/1994ዓ/ም ለሲዳማ ዞን አስተዳዳር በተጻፈ ደብዳቤ መብቱን በሠላማዊ መንገድ ለማስከበርና ያለበትን ጥያቄ ለመንግስት ለማቅረብ መነሻው ገባህላዊ ህዝብመሰብሰቢያ ከሆነው ቱሉ ቦታ በማድረግ በመስቀል አደባባይ የሚያበቃ ሠለማዊ ሰልፍ ስለሚያደረግ የአካባቢው አስተዳዳር ለሰልፉ ጥበቃእንዲያደርግ አመልክቶ ነበር፡፡
ዜጎች መብታቸውን በሠላማዊ መንገድ መጠይቅ ይችላሉ ተብሎ በህገ መንግሰቱ ስለተደነገገ ድንጋጌው የሁሉንም ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችንበእኩል ያስከብራል ብሎ በሙሉ እምነት ተቀብሎ ሰልፍ የወጣው ህዝብ የሰልፉን ደህንነት መጠበቅ የሚገባው ከህዝብ አብራክ የወጣ ህዝብንናየሀገርን ደህንነት ለመጠበቅ ቃል ኪዳን የገባው ሠራዊት በገዛ ወገኑ ላይ በጠራራ ፀኃይ የአውቶማቲክ መሳሪያ ውርጅብኝ አወረደ፡፡
የሠላም ተምሳለት የሆነውን ኢትዮጵያ ባንድራ በማስቀደም ቅጠል የያዘው ህዝብ ከልጅ እስከ አዛውንት በደቂቃዎች ልዩነት እንደ ቅጠል ረገፈ፡፡የተወሰኑ አስከረኖች በአይሱዙ መኪና በላይ ላይ ተደርቦ እንደ ኩንታል ተጭኖ ወደ ሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያ የተጋዘ ሲሆን ሌላው በየጥሻው ተጥሎበጅብ ተበላ፡፡
ይህን ጭፍጨፋ እጅግ ክፉ የክፉ ሁሉ ክፉ እንዲሆን ያደረገው ድርጊት ቀጥሎ መፈፀሙ በሲዳማ ህዝብ አህእምሮ የማይፋቂ የዘላላም ጠባሳ ጥሎአለፈ፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ምን ይሁኑ
1. የሟቾችንን ቤተሰብ በሀይል በማስገደድ አስከሬኖቹን በሟቾች ላይ የተወሰደው እርምጃ አግባቢ ነው እያሉ እየፈረሙ አስከሬኑን እንዲወስዱመደረግ፣
2. በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ቢቢሲን ጨምሮ ሰው አልተገደለም የተገደሉት ዘራፊዎችና ወሮበሎች ናቸው እያሉ ጭፍጨፋው ከተፈፀመበት ቦታ 5ኪ ሜትር ርቀት ላይ ያሉ ህንጻዎችን በኢትቪ በማሳየት አሳፋሪ ድረጊት መፈፀሙ፣
3. ገዳዮችን ለህግ ከማቅረብ ይልቅ ሹመት እየሰጡ ከሞት የተረፉትን ንጽሃን ዜጎችን ለእስራት እንግልት መዳረግ የተቀሩት የብሔሩ ምሁራን ሀገርለቀው እንዲሰደዱ የተደረገበት ድርጊቶች በሀዘን ልቡ ተሰብሮ አጽናኝ ያጣውን ህዝብ ቅስሙ ይበልጥ እንዲሰበር አድርጓል፡፡
በዚህ የተነሳ ነው ይህ ቀን በመላው ሲዳማ ህዝብ አእምሮ ውስጥ የማይጠፋ ጠባሳ ሆኖ የታተመው፡፡ ይህ ቀን በሀገር ውስጥ ባሉና በውጭ ሀገርበሚገኙ በብሔሩ ልጆች ዘንድ ጥቁር የሀዘን ልብስ በመልበስ ሻማ በማብራት እየታሳበ ዘንድሮ 12ኛ ዓመት ላይ የደረሰ ሲሆን ሲዳማ አርነት ንቅናቄበዚህ ዓመት በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን ለማስከበር ሲሉ ሰማእታት የሆኑት ጀግኖችን ልዩ በሆነ መንገድ በሰላማ ሰልፍ ለማሰብ ሠላማዊ ሰልፍጥያቄ ለአካባቢው አስተዳደር ያቀረበ ቢሆንም ወቅቱ ክልላዊና ብሔራዊ ፈተናዎች የሚሰጡበት በመሆኑ ለሰልፉ እውቅና አንሰጥም ተብሎከአካባቢው አስተዳደር እውቅና በመነፈጉ ሠላማዊ ሰልፉ ወደ ሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ/ም እንዲተላለፍ ተደርጓል፡፡
ሲአን ይህ ቀን በሰላማዊ ሰልፍ ታስቦ እንዲውል የመረጠው መንግስት የሲዳማን የመብት ጥያቄ ለማፈን ባሰማራው ፀጥታ አስከባሪ ሰራዊትበተወሰደው እርምጃ በዜጎች ላይ የተከሰተው ጥፋት ሁለተኛ እንዳይከሰት ከመታቀብ ይልቅ በተመሳሳይ መልኩ በኦሮምያ ክልልና በሌሎች በሀገሪቱክፍሎች እየፈፀም ያለው ድርጊት እንዲቆምና ጥፋተኞችም በህግ እንዲጠየቁ ድምጽ ለማሰማት ነው፡፡
ይህ የሰማዕታት ቀን ሰልፉ ስለቀረ ሳይታሰብ ይውላል ማለት ሳይሆን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ከዚህ በፊት ይደረግ እንደነበረ በሁሉም ሲአን ጽ/ቤቶችጥቁር የሀዘን ልብስ በመልበስና ሻማ በማብራት ታስቦ የሚውል መሆኑን እገልጻለሁ፡፡
By ለገሰ ዋንሳሞ ዋቃዮ, Hawassa, Sidama
No comments:
Post a Comment