በየጊዜው ኦሮሞን በመጉዳት የሚታወቀው አቶ ኩማ ደመቅሳ ለሲዳማ ህዝብ ምን እየደገሱ ይሆን?
BY HHH, From Sidama capital Hawassa, May 13, 2014
(https://www.facebook.com/hagerselamh?fref=nf)
መቼም አብዛኛዎቹ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከሁሉም (ወከልን የሚሉትንም ህዝብ ጭምር) በላይ ለመንግሥታቸው የማድላት የ”ዴሞክራሲያዊማዕከላዊነት” ግዴታ እንዳለባቸው ግልፅ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የራሳቸውን ሀሳብ በድርጅቱ የማፀባረቅ መብት የለላቸውና ደፍሮም ከሞከሩ በከፍተኛ”ግለ ህስ” ይቅርታ የሚወርድላቸው (ከኢህአዴግ ማለቴ ነው) እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለዚህም ጥሩ ምሳሌ ሊሆን የሚችለው ደግሞ የኢፌዴሪ የውጭጉዳይ ሚኒስቴሩ ዶር ቴደሮስ አድሐንሆም ናቸው፡፡
ኢኚ ግለሰብ/ባለስልጣን ከአረብ ተጎድተው የተመለሱትን ኢትዮጵያውያንን ቦሌ ሄደው ሲጎበኙ በተሰማቸው ሲሜት(ሰውም አይደል?) ተነሳስተውየአረቡን አለም በመኮኑን የደረሰበትን የማስጠንቀቂያ መዓት በተለያየ አጋጣሚ ለማንበብ ችለናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ምክንያት(”ዴሞክራሲያዊማዕከልነት”) ይሁን በጭካኔ በማይታውቅ መልኩ አቶ ኩማ ደመቅሳ የኦሮሞን ህዝብ ብቻ ሳይሆን መሬትም ጭምር እንደሚጎዱና አንድም ቀንለኦሮሞ ብሔር ብሎ የመንግስት አጀንዳን ስከራከሩ(ዝመታ ሲመርጡ) ተሰምተው/ታይተው አይታወቁም፡፡
ሁሌ መንግስት ትክክል ነው፤ ህዝብ ጥፋተኛ ነው የሚል ፍልስፍና የሚከተሉ የአላዋቂ አዋቂ ናቸው የምሉሏቸውም አልጠፉም፡፡
ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ከተፍተኛ ተምህርት ተቋማት ስለተነሳው የመብት ጥያቄና በምላሹም በመንግስት ስለተወሰደው ጭካኔ የተሞላበትርምጃ አቶ ኩማ ግምባር ቀደም የማጥቃት ድርሻ ይወስዳሉ፡፡
እኛም ይህ ግለሰብ/ባለስልጣን በኦሮሚያ ቴሌቪን ቀርቦ ስለሰጠው አንገተ ደንዳና የመንግስት አቋምና ህዝብን ወንጀለኛ የሚያደርግ ንግግሩን ሰማን፤አነበበን፡፡
ኢኚ ባለስልጣን በትላንትናው (4/09/06ዓ.ም) ቀን ሀዋሳ ገብቶ ከ”ደቡብ” ክልልና ሲዳማ ዞን ባለስልጣናት ጋር በቤተመንግስት ተገናኝተው ሰፊ ጊዜወስደው ተነጋግረዋል ፡፡
ከታማኝ ምንጬ ለማውቅ እንደቻልኩት ግለሰቡ ስለሲዳማ ዞን፣ ወረዳወችና ቀበሌያት ጭምር ሳይቀር ዝርዝር መረጃ እንዲሰጡት የዞንና ክልልባስልጣናትን ቀስረው ይዞ እንደቆየ ሊታወቅ ተችለዋል፡፡
ጥያቄ፡
1. ኩማ የኦሮሞን ህዝብ በማጥቃት ያካበቱትን ዘዴ ሊያካፍሉ ይሆን የተላኩት??
2. ግንግማ ውስጥ “እራሱን ስቶ ወደቀና ሞተ” ስለተባለው ባለስልጣን ሊያጣሩ ይሆን በኃይለማሪያም የተላኩት??
3. “ሐዋሳም አንደ ፊንፈኔ ከአጎራባች ከተሞች ጋር ትተሳሰራለች” የሚል ዜና ባለፎ ሳምንት ተሰምተው ነበር፡፡ ታዲያ አቶ ኩማ በያዘ(ፊንፈኔንበጀመረው) እጅህ ጨርስ ተብሎ ይሆን ወደ ሀዋሳ ያቀናው??
4. “ከተሞችን በፕላን ማስተሳሰር” የሚል ጭንብል የለበሰ የ“ሜትሮፖለታን” አጀንዳ ኩማን ጋልበው እንደገና ሀዋሳ ገብቶ ይሆን??
BY HHH, From Sidama capital Hawassa, May 13, 2014
No comments:
Post a Comment